+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በተካሄደ የዱላ ቅብብል ሩጫ ውድድር ላይ ባለስልጣኑ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቀቀ

ቅድሚያ ለደህንነቶ! በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣንና አይ.ኤፍ.ኤች ኢንጂነሪንግ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የጎዳና ላይ የዱላ ቅብብል ሩጫ ውድድር ተካሄደ፡፡

ይህ የ2022ቱ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር 8 ኪ.ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ውድድሩ በዘመናዊ መልኩ ተገንብቶ ለትራፊክ ክፍት በሆነው ከፑሽኪን አደባባይ-ጎፋ ማዞሪያ -ጎተራ ማሳለጫ መንገድ ላይ ተካሂዷል፡፡ በውድድሩ ላይ የተሳተፈው የባለስልጣኑ የአትሌቲክስ ቡድንም በመንግስት ዘርፍ የሶስተኛ ደረጃነትን ይዞ በማጠናቀቅ የሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኗል፡፡

መንገዶች ለታለመላቸው አገልግሎት እንዲውሉና የመንገድ ደህንነት የሁሉም ጉዳይ እንዲሆን ለማስቻል በስፖርታዊ ውድድሮች ላይ መልክቶችን በማስተላለፍ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር አልሞ የተዘጋጀ ነው፡፡

ለአሸናፊዎች ሽልማቱን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ፣ አትሌት ሺ አለቃ ሀይሌ ገ/ስላሴና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ናቸው፡፡

በመንገድ ደህንነት ላይ ትኩረት ያደረገው ይህ የሩጫ ውድድር በየአመቱ በከተማዋ የተለያዩ ጎዳናዎች ላይ ለረጅም ዓመታት ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በውድድር መድረኩ ላይ መንግስታዊ ተቋማት፣ ኤማባሲዎች፣ ባንክና ኢንሹራንስ፣ መንግስታዊ ያልተሆነ ተቋማት፣ የወጣቶች በጎ ፈቃድ ማህበራት፣ ሆቴልና ጂም አገልግሎት የሚሰጡና ሌሎችም በርካታ ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.