የመንገድ ጥገና ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል
መስከረም 26 ቀን 2015ዓ.ም አዲስ አበባ ፡- የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ የመንገድ ሽፋን ለማሳደግ እና ፍሰቱን የተሳለጠ ለማድረግ በብልሽት ምክንያት ለትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ ያልሆኑ መንገዶችን በመለየት መጠነ ሰፊ የጥገና ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
ባለስልጣን መስርያ ቤቱ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች በክረምት ወራት በሚከሰት ጎርፍ እና ረጅም ዓመታት አገልግሎት በመስጠት ጉዳት የደረሰባቸውን መንገዶችን በመለየት እንደ ጉዳት መጠናቸው ጥገና ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
የቤዝ ኮርስ እና የአስፋልት ጥገና እየተከናወነባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ከኤልያና ሆቴል -ቴዎድሮስ አደባባይ- ብሄራዊ፣ ፈረንሳይ ኪዳነምህረት እንዲሁም ጀርመን አደባባይ ይገኙበታል፡፡
የመንገድ ጥገናው በአብዛኛው በለሊት ክፍለ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን ይህም የከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዳያስተጓጉል ታስቦ የጥገና ስራው እየተከናወነ ይገኛል፡፡
በቀጣይ የከተማዋን የትራፊክ ፍስት ምቹ ለማድረግ ባለስልጣን መስርያ ቤቱ መሰል የመንገድ ጥገና ስራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity