ጎርፍ የከተማችን ችግር በማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ የከተማችን ነዋሪ ተሣትፎ ወሳኝ ሚና አለው።
ከክረምቱ ወቅት ጋር ተያይዞ በባለፉት አመታት በከተማዋ በወንዝ ዳርቻዎች፣ በተዳፋት ቦታዎች፣ ጎርፍ ከፍተኛ ስጋት ሆኖ ቆይቷል፡፡
በመሆኑም ከተማ አስተዳደሩ በዘንድሮ ክረምት ተመሳሳይ አደጋ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ እንዳያጋጥም ከፍተኛ የጎርፍ ስጋት ያለባቸው እና ተጋላጭ ቦታዎችን በመለየት እየሰራ ይገኛል::
ከተማ አስተዳደራችን የጀመረው ሥራ ውጤታማ የሚሆነው በጋራ ስንረበረብ ነው። በወንዞች ዳርቻ የሚኖሩ ተጋላጭ ማህበረሰቦችን ለመነሳት” ዝግጁ መሆንን፥ በወንዝ ውስጥ የተጣሉ ቀሻሻዎችን እና የተደፉ አፈርን በማንሳትና ማጽዳት፥ የወንዝ ዳርቻዎችን በእጽዋት በመሸፈን ቱቦዎችን በማፅዳት ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ይጠበቃል።
እኔም የድርሻዬን እወጣለሁ! ዋናው መርሃችን መሆን ይገባል። ተባብረን ጎርፍ ለከተማችን ችግር በማይሆንበት ደረጃ እናደርሳለን።