የአውጉስታ – ወይራ የመንገድ ፕሮጀክት የገጠመው የወሰን ማስከበር ችግር በመፈተታት ላይ ይገኛል
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም፡- ከአውግስታ- ወይራ መጋጠሚያ ድረስ እየተገነባ በሚገኘው የመንገድ ፕሮጀክት ላይ ለረጅም ጊዜ ለግንባታ ስራው እንቅፋት ፈጥሮ የቆየው ችፑድ ፋብሪካ በመነሳት ላይ ይገኛል፡፡
ከመንገድ ፕሮጀክቱ 300 ሜትር ገደማ የሚሆነው በወሰን ማስከበር ችግር ምክንያት የግንባታ ስራ ለማከናወን አዳጋች ሆኖ ቆይቷል፡፡ ከችቡድ ፋብሪካው በተጨማሪም ሌሎች የመንግሥትና የግለሰብ ቤቶች ከመንገድ ፕሮጀክቱ የወሰን ክልል ውስጥ ሙሉ በሙሉ ባለመነሳታቸው የግንባታ ሂደቱን እዘግይተውታል፡፡
አሁን ላይ የመንገድ ፕሮጀክቱ ካለው አጠቃላይ 1.4 ኪሎሜትር ርዝመት ውስጥ 600 ሜትር የሚሆነው የሰብ ቤዝ እና የከርቭ ስቶን ስራዎች የተጠናቀቁ ሲሆን 500 ሜትር የሚሆነው በመንገዱ የግራ አቅጣጫ በኩል ደግሞ የድሬኔጅ፣ የአፈር ቆረጣ፣ የድጋፍ ግንብ እና የገረጋንቲ አፈር ሙሌት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ አሁን ላይ የመንገድ ፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈፃፀምም 39 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡
ይህን የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ቲ.ኤን.ቲ ኮንስትራክሽን ከ308 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየገነባው የሚገኝ ሲሆን ኦሜጋ ኮንሰልቲንግ የተባለ አማካሪ ደርጅት ደግሞ የማማከር እና የቁጥጥሩን ስራውን እየተከታተለው ይገኛል፡፡
የመንገዱ ግንባታ ሲጠናቀቅ ከጦር ኃይሎች ወደ ቶታል ከሚወስደው መንገድ በስተቀኝ በመታጠፍ በአውግስታ ወደ ወይራ፣ ቤተል አደባባይ፤ እንዲሁም ከአውግስታ በወይራ መጋጠሚያ ወደ ዘነበ ወርቅና አየር ጤና አደባባይ ለመሄድ አማራጭ መንገድ በመሆን ያገለግላል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ :-
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር : https://twitter.com/አባባጭትይ
ዩ-ቲዩብ : https://m.youtube.com/channel/UCylJ2yBcsMuIWIz6nSIjfpQ