የበሻሌ ኮንዶሚኒየም የመንገድ ግንባታ አስፋልት የማንጠፍ ስራ እየተከናወነ ይገኛል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10 ቀን 2014 ዓ.ም፡- ከ324.3 ሚሊዮን ብር በላይ እየተገነባ የሚገኘው የበሻሌ ኮንዶሚኒየም የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የአስፋልት ንጣፍ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
አሁን ላይ 1.2 ኪ.ሜ የሚሆነው የመንገዱ ክፍል የአስፋልት ማንጠፍ ስራ የተከናወነ ሲሆን በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥም 2.8 ኪ.ሜ ድረስ ያለውን የመንገዱን ክፍል አስፋልት በማልበስ ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ቀሪው 700 ሜትር ገደማ ደግሞ በገረጋንቲ አፈር ሙሌት ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ያልተጠናቀቁ የወሰን ማስከበር ስራዎች በመኖራቸው የግንባታ ስራው ላይ አሉታዊ ጫና አሳድሯል፡፡
ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አጠቃላይ 3.5 ኪ.ሜ ርዝመትና ከ15 እስከ 20 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት አለው፡፡
የመንገዱን ግንባታ እያከናወነ የሚገኘው ጥላሁን አበበ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የተባለ ሀገር በቀል ድርጅት ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ጎጎት ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ እየተከታተለው ይገኛል፡፡
ባለስልጣኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በቂ የመንገድ መሰረተ ልማት እንዲኖራቸውና የነዋሪዎችንም ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስር ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads