ከቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚኒየም ወደ ውጨኛው ቀለበት መንገድ የሚያገናኘው የመንገድ ግንባታ የአስፋልት ማንጠፍ ስራ እየተከናወነ ይገኛል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በበጀት ዓመቱ እያስገነባቸው ከሚገኙ በርካታ የመንገድ ፕሮጄክቶች መካከል አንዱ የሆነውና ከቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚኒየም ወደ ውጨኛው ቀለበት መንገድ የሚያገናኘው የመንገድ ግንባታ የአስፋልት ማንጠፍ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
አሁን ላይ ፕሮጀክቱ ካለው አጠቃላይ 1.4 ኪሎ ሜትር ርዝመት ውስጥ 1.1 ኪሎ ሜትር በሚሆነው የግራ መስመር ላይ የአስፋልት ማንጠፍ ስራ በመገባደድ ላይ ይገኛል፡፡
ቀሪው 300 ሜትር የመንገድ ፕሮጀክቱ የግራ ክፍል ላይ ደግሞ የገረጋንቲ አፈር ሙሌት ስራ የተከናወነ ሲሆን በቀጣይ አጭር ጊዜ ውስጥም አስፋልት የማንጠፍ ሰራ የሚከናወን ይሆናል፡፡
በመንገድ ፕሮጀክቱ የቀኝ መስመር ክፍል ቀሪ የመንገድ ግንባታ ሥራዎችን ለማከናወን የወሰን ማስከበር ሥራ አለመጠናቀቁ ለግንባታ ሥራው መዘግየት ምክንያት ሆኗል፡፡
የዚህ መንገድ ግንባታ ፕሮጄክት ስራ ድሪባ ደፈረሻ የተባለ የስራ ተቋራጭ ከ185 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ዋጋ እያከናወነው ሲሆን የማማከርና የግንባታ ቁጥጥሩን ደግሞ ጎንድዋና አማካሪ ድርጀት እየተከታተለው ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ :-
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር : https://twitter.com/Ababacity
ዩ-ቲዩብ : https://m.youtube.com/channel/UCylJ2yBcsMuIWIz6nSIjfpQ