+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከጎጃም በረንዳ ወደ ዮሀንስ ቤተክርስቲያን የሚወስደው መንገድ በጥገና ላይ ነው

ሰኔ 9 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከጎጃም በረንዳ ወደ ዮሀንስ ቤተክርስቲያን የሚወስደውን መንገድ በመጠገን ላይ ነው፡፡

የሕብረተሰብን የጥገና ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት በሚያስችል መልኩ እየተከናወነ ያለው የጥገና ስራ 300 ሜትር ርዝመትና በግራና በቀኝ 9 ሜትር ስፋት የሚሸፍን ነው፡፡

በአካባቢው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች ከዚህ ቀደም መንገዱ በጣም የተጎዳና ለተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ምቹ ባለመሆኑ በተደጋጋሚ ለአደጋ ይጋለጡ እንደነበር አስታውሰው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ችግሩን ተመልክቶ መንገዱን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ መጠገኑ በጣም እንዳስደሰታቸውና በቀጣይም መንገዱ ጉዳት እንዳይደርስበት ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመተባበር የበኩላቸውን እንክብካቤ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

የመንገዱ መጠገን ከጎጃም በረንዳ ወደ አዲሱ ገበያ፣ ሱሉልታ፣ ቀጨኔ እንዲሁም ሰሜን ሆቴል ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች የትራፊክ ፍሰት ምቹ የሚያደርግና ፍሰቱንም የተሳለጠ እንዲሆን የሚያስችል ነው፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በቀጣይ የአስፋልት መንገድ የጥገና ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል የክረምቱ ወቅት ከመግባቱ አስቀድሞ የጥገና ሥራ የሚያስፈልጋቸውን አካባቢዎች በመለየት በርካታ የከተማዋን መንገዶች በጥገና ሥራ ለመሸፈን በትኩረት የሚሠራ ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

Comments are closed.