ለብልሽት የተዳረጉ አጫጭርና አቋራጭ የአስፋልት መንገዶችን በመጠገን የተሻለ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር እየተሰራ ነው
ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በዋና ዋና መንገዶች ላይ እያከናወነ ከሚገኘው የመንገድ ጥገና ስራ ጎን ለጎን ትራፊክ መጨናነቅ ሊያቃልሉ የሚችሉ አቋራጭ መንገዶችን እየጠገነ ይገኛል፡፡
ባለስልጣኑ የከተማውን መንገድ ደረጃ በማሳደግ የተሻለ የትራፊክ እንቅስቃሴ ለመፍጠር የጥገና ስራውን በዋና ዋና እንዲሁም ቀለበት መንገድ ላይ አጠናክሮ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተጎዱ አጫጭርና አቋራጭ መንገዶችን በመለየት በመልሶ ግንባታ ደረጃ የጥገና ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
የጥገና ስራ እየተከናወነባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ቦሌ ቀበሌ 17/19 አካባቢ፣ ከቦሌ ወደ አትላስ የሚወስደው መንገድ በርካታ ኤምባሲዎች ማለትም ባንግላዲሽ፣ አውስትራሊያ፣ ቱርክ፣ ፖርቹጋል እና ደቡብ ሱዳን የሚገኙበት አካባቢ፣ ከጌቱ ኮሜርሻል ህንፃ – ዴሉክስ ፈርኒቸር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ አቋራጭ መንገዶችን በመጠገን በዋና ዋና መንገዶች ላይ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ በመቀነስ የከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴው ምቹ ለማድረግ የጥገና ስራውን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads