+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የቦሌ ሚካኤል- ተሻጋሪ ድልድይ ግንባታ በመፋጠን ላይ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የቦሌ ሚካኤል አደባባይ የላይና የታች መንገድ ቡልቡላ ካባ መግቢያ የመንገድ ፕሮጀክት አንድ አካል የሆነው ተሻጋሪ ድልድይ ግንባታ በመፋጠን ላይ ይገኛል፡፡

አሁን ላይ 600 ሜትር ርዝመት ያለው ተሻጋሪ ድልድይ የግራ መስመርከ 95 በመቶ በላይ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት የተደረገ ሲሆን የቀኝ መስመሩም የቋሚ ምሰስዎቹ ግንባታ ተጠናቆ ዋናውን ድልድይ የመገጣጠም ስራ ተጀምሯል፡፡

ከመንገድ ፕሮጀክቱ አጠቃላይ 5.5 ኪ.ሜ ርዝመት ውስጥ 3 ኪ.ሜ የሚሆነው የአስፋልት ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን አጠቃላይ የፊዚካል አፈፃፀሙም 60.3 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡ ቀሪው 4 ኪ.ሜ ገደማ ደግሞ የከርቭ ስቶን፣የድሬኔጅ እና የገረጋንቲ አፈር ሙሌት ስራዎች ተከናውነው በጊዜያዊነት ለትራፊክ ክፍት ሆኗል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱን አሰር ኮንስትራክሽን ከ936.4 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየገነባው ሲሆን የማማከርና የቁጥጥሩን ስራ ደግሞ ሀይ ዌይ ኢንጂነርስ አማካሪ ድርጅት እያከናወነው ይገኛል፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት ጥቅምት 2012 ዓ.ም በይፋ የተጀመረ ሲሆን 2013 በጀት ዓመት ውስጥ 2.2 ኪ.ሜ የሚሆነው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ በይፋ መመረቁ የሚታወስ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

Comments are closed.