ጠ/ሚ አብይ አህመድ(ዶ/ር)
“አዲስ አበባን ስንመለከት ባለፉት ሶስት አመታት ብቻ 151 ኪ/ሜ አስፓልት ተሰርቷል፡፡ተጠናቆ ስራ ጀምሯል፡፡አንዳንዱ እስከ 60 ሜትር ስፋት አለው፡፡ 151 ሲባል እንደ ገጠር መንገዶች 7 ፤10 ሜትር ሳይሆን እስከ 60 ሜትር ስፋት መንገድ፤ከአስፓልት ውጪ 470 ኪሎሜትር ኮብልስቶን ተሰርቷል አዲስ አበባ ውስጥ፤
አዲስ አበባ ውስጥ ብዙዎች መኪና የላቸውም አስፓልት ብቻ ሳይሆን ሰፋ ያለ የእግር መንገድ ያስፈልጋል ብዬ ነበር 116 ኪሎሜትር ሰፋፊ የእግር መንገዶች ተገንብተዋል፤ ልክ በአራት ኪሎ መንገድ እንደምታዩት በቸርችል ጎዳና እንደምታዩት ወደ ሜክሲኮ እንደምታዩት ሰፋፊ የእግር መንገድ ከዚይ ቀደም በዚያ ስፋትና ጥራት ያልነበረ መንገድ ተገንብቷል፡፡
ይህ ብቻ አይደለም ከተማው ውስጥ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ስላለ ኦቨር ፓሶች ቦሌ ሚካኤል ፤ኢምፔርያል፤መብራት ሃይል አካባቢ እየተፋጠኑ ይገኛሉ፡
ከሳርቤት ጎተራ ያለው 2አመት ተኩል አካባቢ የፈጀው መንገድ አሁን እየተጠናቀቀ ያለው መንገድ በአዲስ አበባ ውስጥ የመጀመርያውን ረጅም ታናል የያዘ ነው፡፡የመጀመርያው ታናል ከፑሽኪን ጎተራ፡፡”
ጠ/ሚ አብይ አህመድ (ዶ/ር)