ለትራፊክ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ የሆኑ የአስፋልት መንገዶች ጥገና ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል
አዲስ አበባ፣ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ለብልሽት የተዳረጉ መንገዶችን በመለየት እየጠገነ ይገኛል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባሳለፍነው ሳምንት ለገሀር፣ ፖስታ ቤት አካባቢ፣ ደምበል ጌቱ ኮሜርሻል ጀርባ፣ ከዓለም ባንክ ወደ አልፋ ት/ቤት እና ከዓለም ባንክ – ስልጤ ሰፈር እና በሌሎች አካባቢዎችም የአስፋልት ጥገና ስራ አከናውኗል፡፡
አሁን ላይ የጥገና ስራ ለማከናወን እቅድ ተይዞ የተግባር እንቅስቃሴ ከተጀመረባቸው አካባቢዎች መካከል ከካዲስኮ ወደ ሀና ማሪያም በሚወስደው ቀለበት መንገድ ላይ፣ ጥቁር አንበሳ አካባቢ፣ ከአትላስ – ቦሌ መድሀኒያለም፣ ልደታ ፍርድ ቤት አካባቢ እና ሌሎችም ቦታዎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ባለስልጣኑ የክረምቱን የጎርፍ ስጋት ለመቀነስ በተለያዩ ቦታዎች የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና የግንባታ ስራዎችን ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads