+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የቄራ – ጎፋ መብራት ኃይል የመንገድ ግንባታ በመፋጠን ላይ ነው

አዲስ አበባ – ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የቄራ ከብት በረት – ጎፋ መብራት ሀይል ኮንዶሚኒየም የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል፡፡

የግንባታ ስራው በወሰን ማስከበር ምክንያት ለረጅም ጊዜ ተጓትቶ የቆየው ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አሁን ላይ 1.85 ኪ.ሜ የሚሆነው የመንገዱ ክፍል የአስፋልት ማንጠፍ ስራ ተጠናቋል፡፡

ከብት በረት አካባቢ 150 ሜትር እና ጎፋ መብራት ኮንዶሚኒየም ጫፍ ላይ 140 ሜትር በድምሩ 290 ሜትር የሚሆነው ቀሪው የመንገዱ ክፍል ደግሞ የሰብ ቤዝና የቤዝ ኮርስ ስራ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን በአጭር ቀናት ውስጥም የሁለተኛ ደረጃ የአስፋልት ስራ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው፡፡

ከዚሁ ጎን ለጎን የእግረኛ መንገድ እና የመንገድ ዳር መብራት ተከላና ተያያዥ ስራዎችም ተጠናቀው አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡

የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ አጠቃላይ 2.14 ኪ.ሜ ርዝመትና 30 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን የግንባታ ስራውን ሜልኮን ኮንስትራክሽን የተባለ የስራ ተቋራጭ ከ214 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እያከናወነው ይገኛል፡፡

የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ቤስት አማካሪ ድርጅት እየተከታተለው ሲሆን አሁን ላይ አጠቃላይ የግንባታ አፈፃፀሙም 66 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡

የዚህ መንገድ ግንባታ ሲጠናቀቅ ከሜክሲኮ በቄራ በኩል አድርጎ ወደ ጎፋ መብራት ኃይል እና አካባቢው ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ በተሻለ ሁኔታ ለማሳለጥ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ :-

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/አባባጭትይ

ዩ-ቲዩብ : https://m.youtube.com/channel/UCylJ2yBcsMuIWIz6nSIjfpQ

Comments are closed.