+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ -ጎሮ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ እየተፋጠነ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም፡- ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ -ጎሮ አይ .ሲ .ቲ ፓርክ ድረስ እየተገነባ የሚገኘው የመንገድ ፕሮጀክት በተሻለ የግንባታ አፈፃፀም ላይ ይገኛል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ 4.9 ኪ.ሜትር ርዝመትና ከ 30 እስከ 60 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት ያለው ሲሆን 1.3 ኪ.ሜ ሜትር የሚሆነው የመንገዱ ክፍል የእግረኛ መንገዱን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል፡፡

አሁን ላይ በመንገዱ የቀኝ ክፍል ላይ 800 ሜትር ተጨማሪ የአስፋልት ማንጠፍ ስራ የተከናወነ ሲሆን 700 ሜትር ደግሞ በሰብ ቤዝ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ በቀጣይ ጥቂት ቀናት ውስጥም የአስፋልት ስራው የሚከናወን ይሆናል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስም ቀደም ሲል የተጠናቀቀውን የመንገዱን ክፍል ጨምሮ 3 ኪሎ ሜትር የሚሆነውን የመንገዱን የቀኝ ክፍል አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩልም አንፃራዊ የወሰን ማስከበር ችግሮች ማነቆ የሆኑበት የመንገድ ፕሮጀክቱ የግራ ክፍል ላይም ከወሰን ማስከበር ነፃ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት የድሬኔጅ መስመር ዝርጋታ፣ የአፈር ቆረጣ እና የሙሌት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

በሌላ በኩል ከአዲሱ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የመኖሪያ መንደር እስከ ጎሮ ድረስ ያለው የመንገድ ፕሮጀክቱ ክፍል በወሰን ማስከበር ባለመጠናቀቁ ምክንያት ምንም ዓይነት የግንባታ ስራ አልተጀመረበትም፡፡

የዚህን መንገድ ግንባታ ሥራ አሰር ኮንስትራክሽን ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እያከናወነው ሲሆን ዩኒኮን አማካሪ ድርጅት ደግሞ የማማከርና የቁጥጥሩን ስራ እየተከታተለው ይገኛል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱን ግንባታ ሙሉ ለሙሉ በለማጠናቀቅ እስከ 24 ወራት የሚደርስ የጊዜ ገደብ የተያዘለት ሲሆን የግንባታ ስራው መጋቢት ወር 2013 ዓ.ም በይፋ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ :-

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/Ababacity

ዩ-ቲዩብ : https://m.youtube.com/channel/UCylJ2yBcsMuIWIz6nSIjfpQ

Comments are closed.