+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከቂርቆስ ወደ ጎፋ ማዞሪያ የሚወስደው ማሳለጫ ድልድይ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል

አዲስ አበባ፡- ሰኔ 3 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የፑሽኪን አደባባይ ጎፋ ማዞሪያ -ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት አንድ አካል የሆነው ከቂርቆስ ወደ ጎፋ ማዞሪያ የሚወስደው ማሳለጫ ድልድይ ግንባታው ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል፡፡

የፑሽኪን አደባባይ ጎፋ ማዞሪያ -ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት አሁን ላይ አጠቃላይ አፈፃፀሙ 96.56 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡

ባለስልጣኑ ቀሪ ስራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ሙሉ በሙሉ ለትራፊክ አገልግሎት ክፍት ለማድረግም እየሰራ ይገኛል፡፡

የዚህ መንገድ ፕሮጀክት የግንባታ ስራ መስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም በይፋ መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ :-

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/Ababacity

ዩ-ቲዩብ : https://m.youtube.com/channel/UCylJ2yBcsMuIWIz6nSIjfpQ

Comments are closed.