+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ለብልሽት የተዳረጉ መንገዶችን በመጠገን የተሻለ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር እየተሰራ ነው

ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በብልሽት ምክንያት ለትራፊክ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ የሆኑ መንገዶችን በመለየት የጥገና ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች ረጅም ጊዜ በማገልገልና በተለያየ ምክንያት ለትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ ያልሆኑ ዋና ዋና እንዲሁም አቋራጭ መንገዶችን በመለየት እንደብልሽት መጠናቸው ቀላልና በመልሶ ግንባታ ደረጃ የአስፋልት ጥገና ስራዎችን እያከናወነ ነው፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የጥገና ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ሩዋንዳ አየር አምባ ት/ቤት አካባቢ፣ ጀሞ አፍሪካ ህንፃ አካባቢ፣ አቃቂ የሺ ቶታል ቱሉዲምቱ አካባቢ፣ ከቀጨኔ 8 ቁጥር ማዞሪያ – ኢትዮ ክሊኒክ፣ ታይዋን ገበያ፣ በርታ ድልድይ አጠና ተራ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

በቀጣይም የመንገድ ጥገና ስራውን በተጠናከረ መልኩ በማስቀጠል የአስፋልት መንገዶችን ደረጃ በማሻሻል የትፊራክ ፍሰቱ የተሳለጠና የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ምቹ ለማድረግ የሚሰራ ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

Comments are closed.