ማስታወቂያ
በመንገድ ግንባታ ምክንያት ዝግ የሚሆን መንገድ ስለማሳወቅ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ እና የተሳለጠ በማድረግ የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማፋጠን በከተማዋ የተለያዩ ማዕዘናት በርካታ የመንገድ ግንባታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በያዝነው በጀት ዓመት የግንባታ ስራቸው ተጠናቆ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት ከተደረጉ መንገዶች መካከል ከወሎ ሰፈር አደባባይ – ወደ ኡራኤል የሚወስደው መንገድ አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ይህ መንገድ በአካባቢው ያለውን የመንገድ መረብ ይበልጥ በማስተሳሰር በኩል ከፍተኛ ድርሻ ያለው በመሆኑ የአካባቢውን የትራፊክ ፍሰት በተሻለ ደረጃ ለማሳለጥ ከወሎ ሰፈር ወደ ኡራኤል አደባባይ መታጠፍ የሚያስችል የትራፊክ መብራት ኡራኤል ቤተክርስቲያን መዳረሻ አካባቢ መትከል አስፈልጓል፡፡
በመሆኑም ከቅዳሜ ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ እስከ ሰኞ ጠዋት ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ከወሎ ሰፈር ወደ ኡራኤል እና ከኡራኤል ወደ አትላስ እና ወደ ወሎ ሰፈር ሚወስዱት መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ሆነው ይቆያሉ፡፡
ስለሆነም አሽከርካሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ከወሎ ሰፈር አደባባይ በቦሌ ሩዋንዳ ወደ አትላስ እና ኡራኤል፤ እንዲሁም ከመገናኛ በ22 ወደ ኡራኤልና አትላስ ለሚሄዱ ደግሞ ከጎላጎል ህንፃ በኤድናሞል በኩል ወደ አትላስ የሚወስደውን እና ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንድትጠቀሙ ባለስልጣኑ ከወዲሁ ያሳስባል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን