የአፍሪካ ህንፃ- መስታዎት ፋብሪካ አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት የግንባታ ስራው በመፋጠን ላይ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24 ቀን 2014 ፣- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ጀሞ ሚካኤል አከባቢ የሚገኘው ከአፍሪካ ህንፃ- መስታዎት ፋብሪካ የሚገናኝ አስፋልት መንገድ ግንባታው በማፋጠን ላይ ነው፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱ 1.68 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 20 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን አሁን ላይ ፕሮጀክቱ ከአጠቃላይ ርዝመት ውስጥ 800 ሜትር ርቀት የሚሸፍነው የመንገዱ ክፍል ላይ የሰብ ቤዝ የማንጠፍ ስራው ሙሉ በሙሉ ከመጠናቀቁም በተጨማሪ የከርቭ ስቶን ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም 40 ሜትር በ 3 ሜትር ስፋት ያለው የካልቨርት ቦክስ ግንባታ ሥራም በመከናወን ላይ ነው፡፡
የመንገዱ ግንባታ ሲጠናቀቅ በዋናነት በጀሞ መንገድ ላይ ያለውን የትራፊክ መጭናነቅ በማቃለል ቀጥታ ከጀሞ ሚካኤል ወደ ቀኝ በመታጠፍ ለቡ እና ፉሪ አካባቢ ለመሄድ በአቋራጭ የትራፊክ መተላለፊያነት የሚያገለግል ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads