+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የተወደዳችሁ የገፃችን ተከታታዮች፤

በየጊዜው ለምታደርሱን አስተያየትና ጥቆማ ያለንን አክብሮት በዚህ አጋጣሚ እየገለፅን፤ ከሰሞኑ ከደረሱን ጥቆማዎች መካከል አንዱ የሚከተለው እንደነበር ልናስታውሳችሁ ወደድን፡-

Yareds Eshetu

”ከቁስቋም እንጦጦ ማርያም የተሰራው አስገራሚ መንገድ የመንገድ ዳር ዘመናዊ መብራት ብዙም ሳያገለግል በብልሽት አገልግሎት መስጠት አቁሟል መፍትሄ ብትሰጡት ። እናመሰግናለን!”

ከፍ ብሎ በተሰጠው ጥቆማ መሰረት ተቋረጦ የነበረው የመንገድ መብራት ችግር ተፈትቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

“ከቁስቋም እንጦጦ ማርያም በአዲሱ መንገድ የመንገድ ዳር ዘመናዊ መብራት በብልሽት አገልግሎት መስጠት አቁሞ የነበረውን ተሰርቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። ለአፋጣኝ ምላሻችሁ እናመሰግናለን!”

እኛም ምስጋናውን በአክብሮት ተቀብለናል፡፡ ወደፊትም አስተያየትና ጥቆማዎቻችሁን ተቀብለን አቅም በፈቀደ መጠን ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት እንተጋለን፡፡

ፎቶ ፡- ከአካባቢው ነዋሪዎች

Comments are closed.