+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የሰሚት 40/60 ኮንዶሚንየም መንገድ ፕሮጀክት አስፋልት ለማልበስ የቅድመ ዝግጅት ስራ በመከናወን ላይ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ፡- የሰሚት 40/60 ኮንዶሚኒየም የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ፕሮጀክት አስፋልት ለማልበስ የቅድመ ዝግጅት ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት በግንቦት ወር መጨረሻ 2013 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን 1 ኪ.ሜትር ርዝመትና ከ8-15 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡ አሁን ላይ 445 ሜትር የሚሆነው የመንገዱ ክፍል የሰብ ቤዝ እና ተያያዥ ስራዎች ተጠናቆው ለአስፋልት ዝግጁ ሆኖ ይገኛል፡፡ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈፃፀምም 38 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡

ይሁን እንጂ ከወሰን ማስከበር ጋር የተያያዙ ሥራዎች በተያዘላቸው ጊዜ ውስጥ ባለመጠናቀቃቸው ምክንያት ግንባታው በታሰበው ፍጥነት እንዳይከናወን ተፅእኖ አሳድሯል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመንገዱ ወሰን ውስጥ የሚገኙ ቀሪ የወሰን ማስከበር ስራዎችን በማጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሲሆን በዋናነት ለሰሚት 40/60 የጋራ መኖርያ ቤት ነዋሪዎች አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ በአካባቢው የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ ለማሳደግ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

Comments are closed.