ስለተሰጠን አስተያየት
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በድልድዮችና በወንዞች ዳርቻ ላይ የሚደፋ የግንባታ ተረፈ ምርት፣ ደረቅ ቆሻሻና መሰል ተያያዥ ችግሮች በመጭው የክረምት ወራት ለጎርፍ መከሰት መንስኤ እንዳይሆኑ ከወዲሁ ድልድዮችን የመጠገንና የማፅዳት ስራ በስፋት እያከናወነ ይገኛል፡፡
ከሰሞኑም በተለምዶ ጀርመን አደባባይ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የድልድይ ጥገናና ፅዳት ስራ መከናወኑን በማህበራዊ የትስስር ገፃችን ማጋራታችን ይታወሳል፡፡ መረጃውን ተከትሎ ከአስተያየት ሰጪዎች ከተነሱ የተለያዩ ሃሳቦች መካከል ለማስተማሪያ ይሆናል ብለን ያሰብነውን አንድ ሀሳብ ወስደን፣ እንዲህ በስፋት እንድንወያይበት እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
Nestanet Asefa
“በእየ ቀኑ እናንተ አሁን እያፀዳችሁ እንኳን ከመኪና ማጠቢያ የሚደፍው ሰጋቱራ የከብት መጫኛ መኪኖች በየ ቀኑ ነው የሚደፉት ስለዝህ የእናንተ ልፍት ነው”
እንደሚታወቀው የባለስልጣን መስሪያ ቤታችን የመንገድ ጥገና መላ ሠራተኞች በየጊዜው የሚገጥሙ ይህን መሰል ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ተከታታይ ስራዎችን በሁሉም የከተማዋ ማዕዘናት እያከናወኑ የሚገኙ ቢሆንም አሁንም አንዳንድ ህገወጥ ግለሰቦች እየፈፀሟቸው ያሉ ያልተገቡ ተግባራት እንደቀጠሉ ናቸው።
እነዚህን ችግሮች በማረም በኩል፦ የመንገድ ሀብቱ ዋነኛ ባለቤትና ተጠቃሚ የሆነው የመላው የከተማችን ነዋሪ ሚና ምን ሊሆን ይገባል?
በከተማችን በተደጋጋሚ እየገጠሙን ያሉ ተመሳሳይ ችግሮችን እንዴት በጋራ እንፍታ? በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ በስፋት ልንወያይበት ይገባል።
ሀሳብ ከመስጠት ባሻገርም በየአካባቢያችን በተግባር የሚገልፁ አርአያነት ያላቸው ተግባራትን በማከናወን ከመጪው የክረምት ወራት ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችለውን የጎርፍ አደጋ ለመቀነስ ድልድዮችንም ሆነ የውሃ መፋሰሻ ቦዮችን በአግባቡና በኃላፊነት በመጠቀም በህዝብና በሀገር ሀብት ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ከወዲሁ መከላከል ይኖርብናል።
በጋራ ጥረታችን፣ ፅዱ፣ ምቹ እና ዘመናዊ አዲስ አበባን እንገንባ!
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads