ናሳው ሪልስቴት አርሴማ ቀለበት መንገድ ፕሮጀክት የአስፋልት ማልበስ ስራ እየተከናወነ ይገኛል
አዲስ አበባ ግንቦት 18 ቀን 2014 ፣- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ እየተገነቡ ካሉ በርካታ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የናሰው ሪል ስቴት መንገድ ፕሮጀክት የአስፋልት ማልበስ ስራ በመከናወን ላይ ነው፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በራስ ሃይል እየገነባው ያለው ይህ የናሰው ሪል ስቴት የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም የግንባታ ስራው መጀመሩ ይታወሳል፡፡ የመንገድ ፕሮጀክቱ አጠቃላይ ርዝመት 1.28 ኪሎ ሜትር ሲሆን 30 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡
ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ከአጠቃላይ የመንገዱ ርዝመት ውስጥ 400 ሜትሩ አስፋልት የለበሰ ሲሆን ቀሪ የመንገዱ ክፍልም የሰብ ቤዝ እና ተያያዥ ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
የመንገዱ ግንባታ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሲሆን ወደ ለቡ ቀለበት መንገድ፣ አንበሳ ጋራጅ ፣ ጀሞ 1፣2፣ 3 የጋራ መኖሪያ መንደሮች እና አካባቢው መሄድ ለሚፈልጉ አሽከርካሪዎች በአቋራጭነት በማገልገል በአካባቢው ላይ ያለውን የትራፊክ ጫና የሚያቃልል ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads