ከገዳመ እየሱስ – 18 መብራት – አጠና ተራ የአስፋልት ጥገና ስራ እየተከናወነ ነው
ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከገዳመ እየሱስ – 18 መብራት – አጠና ተራ የአስፋልት መንገድ ጥገና እያካሄደ ይገኛል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በዋና ዋና እና በአቋራጭ መንገዶች ላይ ከሚያካሂደው የአስፋልት ጥገና ስራዎች በተጨማሪ በቀለበት መንገድ ላይ የተጎዱ ቦታዎችን በመለየት የአስፋልት ጥገና እያካሄደ ይገኛል፡፡
በያዝነው ሳምንት የቀለበት መንገድ አካል የሆነው ከገዳመ እየሱስ – 18 መብራት – አጠና ተራ የጥገና ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡ ይህ መንገድ በቀን ውስጥ በርካታ ተሽከርካሪዎችን የሚያስተናግድ በመሆኑ አልፎ አልፎ በመቦርቦሩ ለትራፊክ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡
በመሆኑም ይህንን ችግር ለመፍታት በቀለበት መንገዱ የፍጥነት እና የመደበኛ መንገዶች ላይ የተጐዳውን የአስፋልት ክፍል ለይቶ በማንሳት የጥገና ስራ ተከናውኗል፡፡ መንገዱ ደረጃውን ጠብቆ መጠገኑ በአካባቢው የሚኖረውን የትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ እና ደህንነቱን የጠበቀ እንዲሆን የሚያስችል ይሆናል።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads