የመዲናችን ጎዳናዎች የምሽት ገፅታ በከፊል
በቢጫና ጥቁር ጉልህ ቀለማት ያሸበረቁት የተሸከርካሪ እና የእግረኛ መተላለፊያ መንገድ አካፋይ የጠርዝ ድንጋዮች(curbstone)፣ እንዲሁም በምሽት ክፍለ ጊዜ በከተማችን ጎዳናዎች ላይ ደማቅ ብርሃን የሚረጩት የመንገድ ዳር መብራቶች፣ የከተማችንን የምሽት ትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ ከማድረጋቸውም በላይ ለመዲናችን ተጨማሪ ውበት አጎናፅፈዋታል፡፡
ወደፊትም የመንገድ ዳር መብራት አገልግሎት በተቋረጠባቸው እና የመንገድ ዳር መብራት ምሰሶ ተተክሎባቸው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ባልተለቀቀባቸው አካባቢዎች የመንገድ ዳር መብራት አገልግለት ተደራሽ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እንሰራለን፡፡
የመንገድ ዳር መብራት አገልግሎት ከሚቋረጥባቸው ምክንያቶች አንዱ በመንገድ ዳር መብራት አካላት ላይ በሚፈፀም ስርቆት ሳቢያ ነውና የመንገድ ሃብታችንን በጋራ እንጠብቅ!
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads