+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የወል ኃላፊነታችንን ለመወጣት አናመንታ!

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የመዲናዋን የመንገድ ሽፋን ለማሳደግና የትራፊክ እንቅስቃሴውን ምቹ ለማድረግ መጠነ ሰፊ የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በዚህ ሂደትም የከተማችንን ገፅታ ትርጉም ባለው መልኩ የቀየሩ ተጨባጭ ለውጦችን ማስመዝገብ ተችሏል፡፡

በዚህ የሚያበረታታ የመንገድ መሰረተ-ልማት ግንባታ ሂደት የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችም ተቋሙ በቀጣይ ጊዜያት ሊያከናውን ላቀዳቸው የመንገድ መሰረተ- ልማት አቅርቦት ስኬት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥሩ ምቹ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

ይሁን እንጂ በከተማችን ውስጥ የተገነቡ መንገዶችን ልክ እንደ ራስ ሃብት በባለቤትነት ስሜት ከመጠበቅ፣ ከመንከባከብና በአግባቡ ከመጠቀም አንፃር በየዕለቱ እዚህም እዚያም የሚታዩ በርካታ ችግሮች በመኖራቸው፣ ከፍተኛ የህዝብና የመንገስት ሃብት ፈሶባቸው የተገነቡ መንገዶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለብልሽት እየተዳረጉ ይገኛሉ፡፡

መንገድ ሁላችንም ያለ ልዩነት፣ በእኩልነት የምንጠቀምበት የጋራ ሃብታችን ነው፡፡ የጋራ ሃብታችንን በጋራ መጠበቅ ደግሞ የሁላችንም ኃላፊነት ነው፡፡ በጋራ ሃብታችን ላይ ጉዳት የሚያደርስ የትኛውም አካልም የጋራ ጠላታችን ነውና ለመታረም ዝግጁ ቢሆን አስተምረን ከጥፋቱ ልንመልሰው፣ ለመታረም ዝግጁ ካልሆነም ከሚመለከታቸው የየአካባቢው የአስተዳደርና የፀጥታ አካለት ጋር በመተባበር በህግ ተጠያቂ ልናደርገው ይገባል፡፡ ምክንያቱም የመንገድ ሃብት ጉዳት በጋራ መጠቀሚያችን ላይ የሚፈፀም ያልተገባ ድርጊት ነውና!

የተሻለ መንገድ፣ ለተሻለች አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

Comments are closed.