የእነዚህ የምትመለከቷቸው ምስሎች ልዩነት ግልፅ ነው፡፡
ከምስሉ እንደታዘባችሁት የመዲናዋ ጎዳናዎች እንደዚህ ባማረና በዘመነ መልኩ ቢገነቡም በአጠቃቀምና ኃላፊነትን በአግባቡ ካለመወጣት የተነሳ የተገነቡበትን አላማ ስተዋል፡፡ በዚህም የተነሳ እግረኛውንና ተሸከርካሪው እኩል በአስፋልት መንገዱ ላይ እየተጋፋ እንዲሄድ አስገድደዋል፡፡ ምክንያቱም የእግረኛ መንገዶቻችን በጋዥና ጎሚስታ ሰራ፣ በጎዳና ላይ ንግድ፣ በግንባታ ቁሳቁስና ተረፈ ምርት ማከማቻነት፣ በሱቅ እቃዎች መደርደሪያነት በነዚህና መሰል ህገወጥ ድርጊቶች ተጠምደዋል፡፡
ስለሆነም የእግረኛ መንገዶቻችን ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የሚመለከታቸው ተቋማትም ሆነ የመዲናዋ ነዋሪዎች ከባለስልጣኑ ጋር በጋራ በመሆን የሚጠበቅባችሁን ኃላፊነት እንድትወጡ ሲል ባለስልጣኑ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ዘመናዊ መንገድ የስልጣኔ መገለጫ ነው!
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ :-
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር : https://twitter.com/አባባጭትይ
ዩ-ቲዩብ : https://m.youtube.com/channel/UCylJ2yBcsMuIWIz6nSIjfpQ