+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ጉዳት በደረሰባቸው መንገዶች ላይ የሚካሄደው የጥገና ሥራ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

ግንቦት 12 ቀን 2014ዓ.ም አዲስ አበባ፡- በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙና ለብልሽት የተጋለጡ የአስፋልት መንገዶች እንደጉዳት መጠናቸው የጥገና ስራ እየተከናወነላቸው ይገኛል፡፡ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተለያዩ የከተማዋ ማዕዘናት እያከናወናቸው ከሚገኙ በርካታአዳዲስ የመንገድ ግንባታ ስራዎች ጐን ለጐን አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ዋና ዋና እና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች መካከል በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ መንገዶችን በመለየት እንደጉዳት ደረጃቸው የጥገና ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡የመንገድ ጥገና ስራ እየተከናወነባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ከኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል – መድኃኒዓለም፣ ከኮካ – አማኑኤል፣ ከአማኑኤል – መሳለሚያ፣ ከታይዋን ዊንጌት፣ ከፖሊስ ሆስፒታል – ልደታ ወረዳ 10 (ዋንዛ ፈርኒቸር)፣ ከሩዋንዳ አደባባይ – ቀለበት መንገድና ሩዋንዳ ኤምባሲ የሚወስዱ መንገዶች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡በዋና ዋና እና በአቋራጭ የአስፋልት መንገዶች ላይ እየተካሄደ የሚገኘው የጥገና ሥራ በአካባቢው የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ ከመቀነሱም በተጨማሪ ምቹ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡

Comments are closed.