+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የፑሽኪን አደባባይ -ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ እሰከዚህ ወር መጨረሻ ድረስ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ይሆናል

ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በስራ ተቋራጭ እያስገነባው የሚገኘው የፑሽኪን አደባባይ – ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ግንባታ ስራ በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ያደርጋል፡፡ይህ የመንገድ ፕሮጀክት 3.8 ኪ.ሜ ርዝመትና ከ30-45 ሜትር የሚሆን የጎን ስፋት ያለው ሲሆን የግንባታ ስራውን ቻይና ፈርስት ሀይ ዌይ ኢንጂነሪንግ ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እያከናወነው ይገኛል፡፡ የግንባታ ቁጥጥሩንና የማማከር ስራውን ደግሞ ቤስት አማካሪ ድርጅት እየተከታተለው ይገኛል፡፡ ከፑሽኪን አደባባይ እስከ ጎተራ ማሳለጫ ያለው ዋና መንገድ ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት የተደረገ ሲሆን አሁን ላይ በተለምዶ ጎፋ ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው የቄራ አካባቢ ከቂርቆስ አቅጣጫ ወደ ጎፋ እና ላፍቶ የሚወስደው ተሻጋሪ ድልድይ መቃረቢያ መንገዶች የመጀመሪያ ደረጃ የአስፋልት ማንጠፍ ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ይህ ዘመናዊ የመንገድ ፕሮጀክት በሁለት በኩል 320 ሜትር ርዝመት ያለው ዋሻ (Tunnel) እና ተጨማሪ የፈጣን አውቶቢስ መተላለፊያ መስመር (Bus Rapid Transit)፣ ከስርና ከላይ መተላለፍ የሚያስችሉ ሁለት ትላልቅ ማሳለጫዎችም አሉት፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ይህን የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ ሙሉ ለሙሉ አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

Comments are closed.