+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የመሰረተ ልማት ቋሚ ኮሚቴ አባላት በግንባታ ላይ የሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አ በባ፣ ሚያዚያ 3 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በግንባታ ላይ የሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ጉብኝቱ የመንገድ ፕሮጀክቶቹን የግንባታ ሂደትና ለግንባታ መጓተት መንስኤ የሆኑ የወሰን ማስከበር ችግሮችን ለመፍታት ያለመ ነው፡፡ባለሰልጣኑ ለመንገድ ግንባታ ስራዎች እንቅፋት የሆኑ የወሰን ማስከበር ችግሮችን ለመፍታት የሚያደርገው ጥረት አበረታች መሆኑን የገለፁት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ ልዕልት ግደይ በቀጣይም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ለማህበረሰቡ ጥቅም ሲባል ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ቋሚ ኮሚቴው እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡በቋሚ ኮሚቴው አባላት የመስክ ምልከታ ከተደረገባቸው የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል ከቃሊቲ ቡልቡላ ቂሊንጦ፣ከአውቶቢስ ተራ መሳለሚያ፣ ከቦሌ ኤር ፖርት ጎሮ፣ ቦሌ ሚካኤል መሻገሪያ ድልድይ፣ ከአውግስታ ወይራ፣ከአራራት ሆቴል ኮተቤ- ካራ እንዲሁም በኮዬ ፈቼ፣ በቦሌ አራብሳ እና በበሻሌ የሚገኙ የጋራ መኖሪያ መንገደሮች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

Comments are closed.