+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የባለስልጣኑ ሠራተኞች ተግባራዊ ዕቅድና ውጤታማ የስራ አፈፃፀም እንዲኖር የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

መጋቢት 29 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- ለአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሠራተኞች በዕቅድ ዝግጅትና ሪፖርት አቀራረብ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያግዝ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፡፡የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስልጠና ማዕከል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኘላንና ልማት ኮሚሽን ጋር በመተባበር የተሰጠው ይህ ስልጠና ከተለያዩ የስራ ክፍሎች ለተውጣጡ 100 መካከለኛ አመራሮችን ያሳተፈ ነው፡፡ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ 50 በመቶ የአፈፃፀም ውጤታማነት የሚመጣው ትክክለኛ እና የተቀናጀ እቅድ ከማቀድ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ በመሆኑም በዕቅድ ዝግጅት እንዲሁም ሪፖርት አቀራረብ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ለባለሙያዎች መሰጠቱ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን እቅድ በተገቢው ሁኔታ ለመፈፀም ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስልጠና ማዕከል ዳይሬክተር ወ/ሮ አበዜ ሱሌይማን ስልጠናው ለሁለት ቀናት የተሰጠ እንደሆነ ጠቅሰው ዓላማው በእቅድ ዝግጅትና ሪፖርት አቀራረብ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ስልጠናውን ከሰጡ ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት አቶ ባዬ ዋናያ የኘላንና ልማት ኮሚሽን በከተማዋ ለሚገኙ 46 ተቋማት የክትትል፣ ድጋፍና ምዘና ስራዎችን እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ ከድጋፍና ክትትል ስራዎች አንዱ የሆነው ስልጠና አቅም መገንቢያ እንደመሆኑ በተለይም እንደዚህ በቀጥታ ስራውን ከሚሰሩ ባለሙያዎች መሰጠቱ ስልጠናውን ውጤታማ ያደርገዋል ብለዋል፡፡ ስልጠናውን የተካፈሉ ባለሙያዎች እንደገለጹት የተሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተግባር ተኮር በመሆኑ በዕቅድ ዝግጅትና ሪፖርት ጥንቅር ዙሪያ የነበሩብንን ክፍተቶች የሚያሳይና ቀጣይ ስራዎችን በእውቀት ለመስራት ትልቅ እገዛ ያለው ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይም መሰል የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናክሮ መስጠት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

23231 ShareLikeCommentShare

Comments are closed.