በስርቆት ወንጀል የተጠረጠሩ የባለሥልጣን መስሪያቤቱ የጥበቃ ሰራተኞች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30 ቀን 2014 ፡- ገርጂ አከባቢ ከሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የብረታ ብረት ወርክ ሾፕ መጋቢት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ላይ ከ 200 መቶ ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው ብረት የሰረቁ ሁለት የጥበቃ ሰራተኞች ክትትል እንዲደረግባቸው ባለሥልጣን መስሪያቤቱ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መሰረት እጅ ከፈንጅ ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል::ባለስልጣኑ በስርቆት ወንጀል የተሳተፉት እነዚህ የጥበቃ ሰራተኞች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ከሚመለከታቸው የፀጥታና የፍትህ አካላት ጋር በጋራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ ወደፊትም የተሰጣቸውን የሥራ ኃላፊነት ወደ ጎን በመተውና እምነት በማጉደል ለግል ጥቅማቸው የሚንቀሳቀሱ ሠራተኞች ቢኖሩ ተከታትሎ ተገቢውን ህጋዊ ቅጣት እንዲያገኙ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንደሚቀጥል እየገለፀ፣ በዚህ የመንግስት ሃብት ዘረፋ ተግባር ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ጥቆማ በመስጠት የዜግነት ኃላፊነታቸውን ለተወጡት የተቋሙ ሰራተኞች ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
27276 Comments3 SharesLikeCommentShare