+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የአያት ጣፎ የማስፋፍያ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ደረጃ አስፋልት ማልበስ ስራ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በራስ ኃይል ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው የአያት- ጣፎ የማስፋፍያ ፕሮጀክት የመጀመርያ ደረጃ የአስፋልት ማልበስ ስራው ተጠናቀቀ ፡፡ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የማስፋፍያ ፕሮጀክቱን ስራ በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም የጀመረ ሲሆን፣ ፕሮጄክቱ በአጠቃላይ 3.8 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 6 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን ነው፡፡ አሁን ላይ የአያት ጣፎ መንገድ ማስፋፊያ ግንባታ የመጀመርያ ደረጃ የአስፋልት ማልበስ ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪ የመንገድ ፕሮጀክቱን ስራዎችም በአጭር ጊዜ ውስጥ በመጠናቀቅ መንገዱን ሙሉ በሙሉ ለትፊክ አገልግሎት ክፍት ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡የማስፋፊያ መንገዱ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ፤ በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ የአዲስ አበባ ከተማ የመውጫና መግቢያ በር በሆኑት በአያት ጣፎ እና በካራ መስመሮች ላይ የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ በመቀነስ በአካባቢው የሚኖረውን የትራፊክ ፍሰት ከማሳለጡም በተጨማሪ ወደ የካ አባዶ እና ጣፎ አካባቢ ለሚጓዙ ተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ይታመናል፡፡

54545 Comments2 SharesLikeCommentShare

Comments are closed.