+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የእግረኛ መንገዶችን በግንባታ ቁሳቁሶች እና ተረፈ ምርቶች በዘጉ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው

መጋቢት 26 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በእግረኛ መንገድ ላይ የግንባታ ግብአትና ተረፈ ምርት በማስቀመጥ ጉዳት እያደረሱ በሚገኙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡ የባለስልጣኑ ማዕከላዊ አዲስ አበባ መንገድ ሀብት አስተዳደር በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የመንገድ መብት ጥሰት በመፈጸም የትራፊክ እንቅስቃሴ ባስተጓጎሉ አካላት ላይ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ሕጋዊ ርምጃ አከናውኗል፡፡ባለስልጣኑ በቀጣይም በመንገድ መሠረተ ልማት ላይ የሚፈፀሙ ህገ-ወጥ ተግባራትን ለመከላከል የሚወሰደው ህጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ህብረተሰቡም በመንገዶች ላይ የሚፈፀሙ የመብት ጥሰቶች ሲያጋጥሙት በነፃ የስልክ መስመር 8267 ደውሎ በማሳወቅ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ ባለስልጣኑ ጥሪውን ያቀርባል።

Comments are closed.