+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከዋቢ ሸበሌ ሆቴል ወደ ቡና እና ሻይ የሚያቋርጥ መንገድ ተገንብቶ ለትራፊክ ክፍት ተደርጓል

የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፤ ከዋቢ ሸበሌ ሆቴል ወደ ቡና እና ሻይ የሚያቋርጥ የመንገድ ግንባታ ስራ አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ፤ በዋና ዋና መንገዶች ላይ የሚፈጠረውን የትራፊክ ጫና ለማቃለል፤ በተለያዩ አካባቢዎች ዋና ዋና መንገዶችን በአጭር ርቀት የሚያስተሳስሩ አቋራጭ መንገዶችን በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

በቅርቡ የግንባታ ስራው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው ይህ መንገድ 180 ሜትር ርዝመት እና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ 15 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡

የመንገድ ግንባታ ሥራውን የባለሥልጣን መስሪያ ቤት የማዕከላዊ አዲስ አበባ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አከናውኖታል።

Comments are closed.