39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ
39ኛውን የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ለመዘገብ ውድ መዲናዋ የመጡ ጋዜጠኞች በአዲስ አበባ ውበት ተገርመዋል፡፡
ለ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ወደ መዲናችን አዲስ አበባ የመጡ የተለያዩ ሀገራት አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች አዲስ አበባ በአዲስ መልክ እና ገጽታ ስለመለወጧ መስክረዋል፡፡
የተለያዩ ሀገራት መገናኛ ብዙሃንን የሚወክሉት እነዚህ የሚዲያ ባለሙያዎች ከተማዋ መንገዶቿን አዘምና ፤ መሰረተ ልማቶችን አሟልታ ለጉበኤው የመጡ እንግዶችን በብቃት እንዳስተናገደች ሲዘግቡ ተሰምተዋል፡፡ ለአብነትም የቻይናው ሲጂቲኤን እና ዥንዋን ጨምሮ ኢመሬት ኒውስ እና ቲአርቲ አፍሪካ የተሰኙ መገናኛ ብዙሃና የከተማዋ ውበት እጅግ የሚያስደንቅ እና ዘመናዊነትን የተለበሰ ምቹ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በከተማዋ የሚገኙ የቱሪስ መዳረሻዎች ሰፋፊ የእግረኛና የተሽከርካሪ መንገድን ጨምሮ ዘመናው እና በቴክኖሎጂ የታገዙ የመንገድ ዳር መብራቶች ለከተማዋ ልዩ ውበት እንዳጎናፀፏት ጋዜጠኞቹ ለአለም መስክረዋል፡፡


Previous Post
Next Post
Users Today : 2
Users Last 7 days : 281
Users Last 30 days : 1205