+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የኮሪደር እና ወንዝ ዳርቻ ልማት አፈፃጸምን በተመለከተ

👉ባለፉት 6 ወራት ከኮሪደር እና ወንዝ ዳርቻ ልማት በተሰሩ ስራዎች ፤- ከአራት ኪሎ – ሽሮ ሜዳ ኮሪደር ፣ የሳውዝጌት-መገናኛ – መስቀል አደባባይ ኮሪደር፣ የሳርቤት- ካርል አደባባይ – አቦ ማዞሪያ – ላፍቶ አደባባይ – ፉሪ ኮሪደር፣ የሲኤምሲ – ሰሚት – ጎሮ – ቦሌ ቪአይፒ ኮሪደር ተጠናቀው ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ተደርጓል፡፡

👉3ሺህ ሄክታር መሬትና 48 ኪ.ሜ ሜትር ዝርመት የሚሸፍኑ 8 የወንዝ ዳርቻ ልማቶች እየተከናወኑ ሲሆን፤ በተለይም 25 ኪ.ሜ በላይ የሚሸፍነው የእንጦጦ ፒኮክ-ካራማራ ድልድይ፣ 2ዐ ኪ.ሜ የሚሸፍነው የቀበና ግንፍሌ እንዲሁም ቁርጡሚ ወንዝ ዳርቻ እጅግ ውብ፣ ጤናማና የቱሪስት መዳረሻ በሚሆን መልኩ ስራወ በፍጥነትና በጥራት 24/7 በመስራት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

👉የተሰሩትን ቁልፍ የሆኑ መሰረታዊ ልማቶች ከማስቀጠል አንፃር መዋቅር በማዘጋጀት የኮሪደርና ወንዝ ዳርቻ ልማት ባለስልጣን ተቋቁሞ ወደ ስራ የተገባውም በዚሁ ግማሽ አመት ነው::

👉ከኡራኤል – አትላስ – ቦሌ ብራስ፣ ከጎላጎል – ኤድናሞል – ፍሬንድሺፕ እና ከውሃ ልማት በአትላስ ሩዋንዳ ድልድይ ኮሪደር ልማት ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

👉አራዳ ፓርክ፣ አራት ኪሎ መኪና ማቆያና የገበያ ማእከል፣ የአራዳ የመኪና ማቆሚያ እና የገበያ ማዕከል እንዲሁም የመኪና ማቆሚያና የድል ፕላዛ ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል፡፡

👉ከነዚህ በተጨማሪ ከመደበኛ እቅዶች በተጨማሪ በኮሪደር ልማት 17 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ፣ 34 ኪሎ ሜትር የእግራኛ መንገድ፣ 13 የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች በመጠናቀቅ ላይ ናቸው፡፡

👉በከተማ ደረጃ ከሚሰራው መጠነ ሰፊ የኮሪደር ልማት በተጨማሪ በክፍለ ከተሞች አቅም በአራዳ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በለሚ ኩራ እና በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተሞችም ተጀምረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Comments are closed.