+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጀርባ በሚገኘው የወንዝ ዳርቻ ልማት እየተገባ የሚገኘው መንገድ አስፋልት የማልበስ ስራ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፤ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጀርባ ባለው የወንዝ ዳርቻ ልማት እየገነባ በሚገኘው መንገድ አስፋልት የማንጠፍ ስራውን አጠናቀቀ፡፡

ግንባታው በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ራስ ኃይል የማዕከላዊ መንገድ ጥገና ፕሮጀክት ጽ/ቤት እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 250 ሜትር ርዝመትና የእግረኛ መንገድ ጨምሮ 10 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን ነው፡፡

አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ የአስፋልት ማልበስ ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ቀሪ የእግረኛ መንገድ ታይልስ ንጣፍና ተያያዥ ስራዎችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ በርብርብ እየተሰራ ይገኛል፡፡

በተመሳሳይም ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ፒኮክ መናፈሻ እየተካሄደ ባለው የወንዝ ዳርቻ ልማት የመንገድ ግንባታ እያከናወነ ይገኛል፡፡

የመንገድ ግንባታው በራስ ኃይል ማዕከላዊ መንገድ ጥገና ፕሮጀክት ጽ/ቤት እየተከናወነ ሲሆን፤ አጠቃላይ ርዝመቱ 650 ሜትርና 7 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ነው፡፡

አሁን ላይ 350 ሜትር የሚሆነው የመንገዱ ክፍል አስፋልት የለበሰ ሲሆን ቀሪውን የመንዱን ከፍል በጥቂት ቀናት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል፡፡

Comments are closed.