+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በ6ኛው የህብረት ስምምነት ሰነድ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከተለያዩ የስራ ክፍሎች ለተውጣጡ ሰራተኞች በ6ኛው የህብረት ስምምነት ሰነድ፣ ማዋሎችና በተለያዩ የአሰራር መመሪያዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አበዜ ሱለይማን እንደገለፁት፤ ተቋሙ በአዲሱ ሪፎርም ተግባራዊ ካደረጋቸው የአሰራር ማሻሻያዎች መካከል በ6ኛው የህብረት ስምምነት ሰነድ፣ አዲ በጸደቁ ልዩ ልዩ ማዋሎችና መመሪያዎች የተደነገጉ የአሰሪውና ሰራተኛው መብትና ግዴታዎችን በተመለከተ ለሰራተኛው በቂ ግንዛቤ በመፍጠር በተቋሙ መልካም የስራ ግንኙነት እንዲዳብር ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ወ/ሮ አበዜ አያይዘውም፤ የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ህብረት ስምምነቱን፤ ልዩ ልዩ ማኑዋሎችና መመሪያዎች በአግባቡ ተረድተው ተግባር ላይ ከማዋል አንፃር የሚታየውን የግንዛቤ ክፍተት በመሙላት ረገድ ስልጠናው መሰጠቱ የሚኖረው ሚና የጎላ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ስልጠናውን የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የስልጠና ዳይሬክቶሬት፣ የሥነ-ምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬትና የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑን የጠቀሱት ወ/ሮ አበዜ፤ ስልጠናው ከህዳር 4 ቀን 2018ዓ.ም ጀምሮ 3150 ለሚሆኑ የባለሥልጣኑ ሰራተኞች በ15 ዙር ለአንድ ቀን እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል፡፡

ለ6ኛ ጊዜ ተሻሻሎ የፀደቀው የህብረት ስምምነት ከመስከረም 2018 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ መዋሉ ይታወሳል።

Comments are closed.