የሬጉላቶሪ ዘርፍ የስራ ክፍሎች የ60 ቀናት ዕቅድ የርክክብ ስነ-ስርዓት
አዲስ አበባ፣ ህዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም፡- ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በቅርቡ ያካሄደውን ሪፎርም የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ የተቋሙ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች የ60 ቀናት ዕቅድ በማዘጋጀትና በዘርፍ ደረጃ አረጋግጠው በማፀደቅ ወደ ትግበራ እየተሸጋገሩ ይገኛሉ፡፡
በዛሬው ዕለትም፤ የባለሥልጣን መስሪያቤቱ የሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በዘርፉ ስር ከሚገኙ 7 የስራ ክፍሎች ጋር የ60 ቀናት ዕቅድ፤ የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር እና የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በታዛቢነት በተገኙበት መድረክ የርክክብ ሥነ-ስርዓት አከናውነዋል፡፡
በሁሉም የባለሥልጣን መስሪያቤቱ ዘርፎች ተረጋግጦ ወደ ትግበራ የተሸጋገረው የ60 ቀናት ዕቅድ፤ የተቋሙን የሪፎርም ሥራዎች ውጤታማነት ለመለካት ከማገዙም በተጨማሪ፣ ለህብረተሰቡ የመንገድ መሠረተ-ልማት ጥያቄ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንደሚያስችል ይታመናል።


Previous Post
Next Post
Users Today : 25
Users Last 7 days : 332
Users Last 30 days : 987