+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

“የመደመር መንግስት”መጽሐፍ ላይ የፓናል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5 ቀን 2018ዓ.ም፡-የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የተጻፈው “የመደመር መንግስት”መጽሀፍ ዙሪያ የባለሥልጣኑ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት የፓናል ውይይት አካሂዷል።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ እንደገለፁት፤ የመደመር መንግስት መጽሐፍ ሀገር በቀል ፍልስፍና እና አስተሳሰብን ወደ ተግባር የሚቀይር ከመሆኑ ባሻገር የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል እሳቤ የያዘ ነው ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፤ የብልፅግና ጉዞ ትልቅ ተስፋ ያየንበት በመሆኑ በሀገርና በትውልድ ግንባታና ብልፅግና ሁሉም የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የውይይቱን መነሻ ሀሳብ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሰላም እና ደህንነት መምህር እና ተመራማሪ ሙሉጌታ አየለ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ የአመራርና አስተዳደር መምህርና ተመራማሪ ታምሩ ፈይሳ (ዶ/ር) ናቸው።

በፖናል ውይይቱ ላይ “የመደመር መንግስት” መጽሀፍ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የትላንትና የዛሬ ማንነት የሚያሳይ፣ የአለም ነባራዊ ሁኔታ የሚዳስስ፣ የሀገሪቷን ቁልፍ ችግሮች በመለየትና በማመላከት ሀገር በቀል መፍትሄዎችን የሚያመላክቱ እሳቤዎችን የያዘ መጽሀፍ መሆኑን በምሁራኖቹ ተገልጿል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ የመደመር ሃሳብ ለሀገር እድገት ብቻ ሳይሆን፤ ለመላው ዓለም አስፈላጊ እና ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፤ መፅሀፉ አዲስ የፖለቲካ እይታ የፈጠረ፣ አብሮነትና መተባበር ለሀገረ-መንግሥት ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ያነሳ ነው ብለዋል።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ቀደም ሲልም መደመር፣ የመደመር መንገድና የመደመር ትውልድ በሚሉ ርዕሶች ተከታታይ መፅሀፍት ማዘጋጀታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ የመደመር መንግስት በሚል ርዕስ ያሳተሙት አራተኛው መጻሀፍ በቅርቡ በደማቅ ሥነ-ስርዓት ተመርቆ ለንባብ መብቃቱ ይታወሳል፡፡

Comments are closed.