+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የመንገድ ጥገና ሥራ እንደቀጠለ ነው

ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያየ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን አስፋልት መንገዶች እየጠገነ ይገኛል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የአስፋልት ጥገና ሥራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል፤ ከዓለም ባንክ ስልጤ ሰፈር፣ ከኮካ አደባባይ አብነት አደባባይ፣ ከአያት አደባባይ – ሰሚት 72፣ ከሰሚት አደባባይ – አያት አደባባይ እንዲሁም ላፍቶ በላይ – ላፍቶ ጊዮርጊስ – ላፍቶ ቪው፣ ከቃሊቲ አደባባይ – አደይ አበባ – ጎተራ ማሳለጫ ይገኙበታል፡፡

ባለስልጣን መስሪያቤቱ በቀጣይም በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙና ጥገና የሚያስፈልጋቸውን መንገዶች በመለየት የጥገና ስራዎችን በስፋት የሚያከናውን ይሆናል፡፡

Comments are closed.