+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በሥነ-ምግባር የታነፀ የሰው ኃይል በመገንባት በኩል የሥራ መሪዎች ድርሻ የጎላ መሆኑ ተገለፀ

በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና የሥራ መሪዎች፤ አርዓያነት ያለው ሰብዕና በመላበስ፣ ብልሹ አሰራሮችን የሚታገልና ሙስናን የሚፀየፍ ተቋማዊ ባህል እንዲጎለብት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

ጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ:- ለአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አመራሮችና የሥራ መሪዎች ዛሬ ከቀትር በፊት በሥነ-ምግባርና ሙስና መከላከል ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አባተ ገብረአምላክ፤ ስልጠናው በተቋሙ ሙስናና ብልሹ አሰራርን የመታገል የሥራ ባህልና ተግባራዊ አፈጻጸም እንዲጎለብት አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረዋል።

በአዲሱ የተቋሙ ሪፎርም ምደባ የተሰጣቸው አዳዲስና ነባር የሥራ መሪዎች በሥልጠናው ተካፋይ መሆናቸውን የገለፁት አቶ አባተ፤ ስልጠናው በተቋሙ ውጤታማ የሃብት አጠቃቀምን በማሳደግ ለተሻለ ተቋማዊ ውጤት ማስመዝገብን ታላሚ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት ከአዲስ አበባ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የአውታሮች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አምባላይ ዘርአይ፤ ስልጠናው በተቋም ውስጥ ስነ-ምግባራዊ ባህልን በማጎልበት ሙስና ስጋት የማይሆንበት ተቋም ለመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

አቶ አምባላይ አክለው ስልጠናው የተቋሙን ተልእኮ ለማሳካት የሙስና ወንጀሎችን ከመከላከል ባለፈ አሳታፊ የአመራር ሥርዓት መፍጠር ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

Comments are closed.