+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ማሳሰቢያ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የግንባታ ሥራ የሚያከናውንባቸውን የፕሮጀክት ሳይቶች እንቅስቃሴ በተመለከተ፤ በባለሥልጣን መስሪያቤቱ የማህበራዊ ትስስር ገፆቹ እና በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በየጊዜው ወቅታዊ መረጃዎች እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል።

ይህም፤ ህብረተሰቡ በግንባታ ሂደት ላይ ስላሉ መንገዶች ቅድመ-ጥቆማ መረጃ እንዲደርሰው ከማስቻሉም በተጨማሪ፣ በአካባቢው የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠርና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም እንዲንቀሳቀሱ እንደሚያስችል ይታመናል።

ይሁን እንጂ አንዳንድ አሽከርካሪዎች ከባለሥልጣን መስሪያቤቱ የሚሰጡ መረጃዎችን ባለመከታተል እና በግንባታ ሥፍራዎች የሚቀመጡ ምልክቶችን ባለማስተዋል፣ በፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የትራፊክ አደጋ የሚከሰትባቸው አጋጣሚዎች ታይተዋል።

አሁን ላይ በከፍተኛ ርብርብ የግንባታ ሥራው በመፋጠን ላይ በሚገኘው የአትላስ – ኤድናሞል – ብራስ ኮሪደር ግንባታ መስመር ላይ የተከሰተው የትራፊክ አደጋም የዚሁ ችግር አንዱ ማሳያ ነው።

በሥፍራው የተከሰተው አደጋ፤ በቦታው የተቀመጠውን የግጭት መከላከያ በመጣስ እና የቅድመ ማስጠንቀቅያ ምልክት ባለማስተዋል የተከሰተ ነው።

በመሆኑም አሽከርካሪዎች፤ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ በመገናኛ ብዙሃን እና በተቋሙ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የሚያስተላልፋቸውን ወቅታዊ መንገድ ነክ መረጃዎችን በመከታተል በጥንቃቄና በእርጋታ እንዲያሽከረክሩ አበክሮ ያሳስባል።

የተሻለ መንገድ፣ ለተሻለች አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

Comments are closed.