ባለፉት 11 ወራት የላቀ አፈፃፀም መመዝገቡ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ጀነራል ካውንስል አባላትና በየደረጃው የሚገኙ የሥራ መሪዎች የ2017 በጀት ዓመት 11 ወራት ዕቅድ አፈፃፀምና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
የውይይት መድረኩን የመሩት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሙህዲን ረሻድ፤ ባለፉት 11 ወራት ከኮሪደር ልማቱ ጎን ለጎን በበጀት ዓመቱ በመደበኛ ስራዎች የታቀዱ የመንገድ ግንባታና ጥገና ተግባራት በቀንና በሌሊት ክፍለ ጊዜ በትኩረት በመከናወናቸው ከዕቀድ በላይ አፈፃፀም ሊመዘገብ መቻሉን አንስተዋል፤ በየደረጃው የሚገኙ የሥራ መሪዎች ኣና ሰራተኞች ያሳዩት የስራ ትጋት የሚደነቅና የሚመሰገን ነው ብለዋል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በክረምቱ ወራት ከሚያከናውናቸው መደበኛ ሥራዎችጎን ለጎን፤ በከተማ ደረጃ በቀጣዮቹ 90 ቀናት ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል11 ግቦችን በመውሰድ በትኩረት እንደሚሰራ ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በራስ ኃይል መንገዶችን በጥራትና በፍጥነት የመገንባት አቅሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱ የሚያበረታታ መሆኑን ጠቁመው፤ በቀጣይም የተቋሙን ውጤታማነት ለማስቀጠል የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ለረጅም ዓመታት በተለያዩ የስራ መስኮች በኃላፊነት ሲያገለግሉ የነበሩ እና አሁን ላይ በሹመት፣ በዝውውርና በጡረታ መስሪያ ቤቱን የለቀቁ የቀድሞ የሥራ መሪዎች አሸኛኘት በዕለቱ የተደረገ ሲሆን፣ ለተሸኚዎቹ የምስጋና የምስክር ወረቀት እና የመታሰቢያ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር (X) ፡- https://twitter.com/AbabaCity
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ
