+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በዛሬው ዕለት ከተማ አቀፍ የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎችን በይፋ አስጀምረናል።

ከለውጡ ወዲህ የበጎ ፍቃደኝነት አገልግሎት የአንድ ወቅት የንቅናቄ ስራ ብቻ ሳይሆን የሁሌ ተግባር እና ባህል ማድረግን ታሳቢ በማድረግ ተቋም መስርተን፣ ተቋማዊ አሰራርን በመዘርጋት ባከናወንነው ስራ የሚሊዮኖች እንባ ታብሷል።

በዛሬው ዕለት ያስጀመርነው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትም የበርካቶች እምባ የሚታበስበት፣ ለአቅመ ደካሞች 2,500 ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶች በመገንባት የዘመሙ ጎጆዎች የሚቃኑበት፣ ለ500,000 ሰዎች ማዕድ በማጋራት የክረምት የኑሮ ጫናን ማለፍ የምናስችልበት፣ ወላጅ የሌላቸዉ 440 ህፃናት አሳዳጊና ተንከባካቢ ቤተሰቦች የሚያገኙበት፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል ከተማችንን አረንጓዴ የምናለብስበት እና ሌሎች በርካታ ስራዎችን የምንሰራበት አያሌ ዝርዝር ተግባራትን ያቀፈ ነው።

በምሳሌነት የምንገልጻችሁ የከተማችን ባለሀብቶች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ተቋማት በሙሉ በተለመደው መልኩ በገንዘባችሁ፣ በጉልበታችሁ እና በእውቀታችሁ አብራችሁን እንድትሰሩ ጥሪዬን እያቀረብኩ፤ እስካሁን ላበረከታችሁት ታሪካዊ አስተዋጽኦ አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Comments are closed.