ባለፉት 11 ወራት ከ1200 ኪሎ ሜትር በላይ የግንባታና የጥገና ስራዎች ተከናውነዋል
የዕቅድ አፈፃፀሙ ከ2016 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀርም የ47 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡
አዲስ አበባ፣ ሰኔ7 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በ2017 በጀት ዓመት ባለፊት 11 ወራት 1,278 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍኑ ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታና የጥገና ስራዎች በማከናወን ከዕቅድ በላይ መፈፀም ችሏል፡፡
ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ 11 ወራት 1121 ኪሎ ሜትር የግንባታና የጥገና ስራዎች ለማከናወን አቅዶ ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን፣ በዕቅድ ከተያዙት ሥራዎች በተጨማሪ በርካታ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች በቀንና በሌሊት ክፍለ ጊዜ በመሠራታቸው የላቀ አፈፃፀም እንዲመዝገብ አስችሏል፡፡
ባለፉት 11 ወራት ከ 314 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት የሚሸፍኑ ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የተገነቡትን መንገዶች ጨምሮ 60 ኪሎ ሜትር የአስፋልት፣ 13 ኪሎ ሜትር የጠጠር እና 74 ኪሎ ሜትር የኮብል ንጣፍ መንገድ ስራዎች ይገኙበታል፡፡
በሌላም በኩል 84 ኪሎ ሜትር ነባር የእግረኛ መንገዶችን ለማዘመን የመልሶ ግንባታ እና 78 የሳይክ መንገድ ግንባታ ከመከናወኑም በተጨማሪ፣ የመንገድ ዳር ውሃ መፋሰሻ መስመሮች ግንባታ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡
ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከግንባታ ስራዎች ጎን ለጎን፣ በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተጋለጡ 100 ኪሎ ሜትር የአስፋልት፣ 20 ኪሎ ሜትር የጠጠር፣ 339 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ መከላከያ አጥር ስራዎች፣ 452 ኪሎ ሜትር የድሬኔጅ መስመሮች ፅዳት፣ 6 ኪሎ ሜትር የድሬኔጅ መስመር ዕድሳትና ጥገና፣ 18 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ ጥገናና የከርቭ ስቶን ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
ከዚህም ሌላ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ 19.7 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮብል መንገድ ጥገና፣ በቁጥር 20 የድልድይ እና የድጋፍ ግንብ ጥገና ስራዎች፣ 3 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መከላከያ አጥር አዲስ ስራና ጥገና በማከናወን በድምሩም 963.3 ኪሎ ሜትር የጥገና ስራዎችን ባለፊት 11 ወራት አጠናቆ ለአገልግሎት አብቅቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር (X) ፡- https://twitter.com/AbabaCity
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ
