+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በመዲናችን 35ኛው የአፍሪካ የሕፃናት ቀን በዓል በተለያዩ ሁነቶች በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ

የቀዳማይ ልጅነት ሣምንት እና በአፍሪካ ለ35ኛ እንደ ሃገር ለ34ኛ ጊዜ”የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ለማነጽ ሕፃናት ተኮር ተግባራትን እናከናውን!” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።

መንግስት ህፃናትን ለማስደግ መዲናችን አዲስ አበባን ምርጧ አፍርካዊት ከተማ በማድረግ ረገድ ቁርጠኛ አቋም ወስዶ ሕፃናት ለሃገር ያላቸዉ ተስፋ እውን እንዲሆን ከማኅፀን ጀምሮ በሚደረግ እንክብካቤ፣ በአልሚ ምግብ፣ በጨዋታ መማር፣ በትምህርት ቤት ምገባ፣ በቤተሰባዊ ትስስር መልካም ዕድገት በማስረፅ፣ ሁለንተናዊ መብቶቻቸዉ ተከብረዉ በሀገራዊ ግንባታ፣ ልማቶች እና ዕድገቶች ውስጥ ተሳትፎአቸዉ እዉን ለማድረግ በርካታ ስራዎችን ሠርቶ ተጨባጭ ለዉጦችን እያስመዘገበ ይገኛል::

በዚህም መሰረት:-

👉በቀዳማይ ልጅነት በ2015፦45 ዘመናዊ የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች

👉በ2016፦277 ዘመናዊ የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች

👉በ2017፦1131 ዘመናዊ የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች

👉ከ2015እስከ 2017 ድረስ በድምሩ፦1453 ዘመናዊ የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች ሲሆኑ

👉በሁሉም ክፍለ ከተማ እና ወረዳ በየሳምንቱ የሚዘጉ 132 የሰንበት ዝግ መንገዶች ከፍተኛ ቀጥር ያላቸው ሕፃናት የሚጫወቱበት፤

👉 በየወሩ በዝቅተኛ የንሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ 11900 ነብሰ-ጡር ሴቶች አጥቢ እናቶችና እድሜያቸው እስከ 3ዓመት ለሆኑ ሕፃናት የቀጥታ አልሚ ምግብ ድጋፍ የሚያገኙበት፤ እንዲሁም

👉በተለያየ 822 በላይ በሆኑ የሕፃናት የቀን ማቆያዎች 15,712 ሕፃናት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ታዉቋል።

Comments are closed.