ቋሚ ኮሚቴው የመስክ ምልከታውን በማጠናቀቅ ግብረ መልስ ሰጠ።
በአዲስ አበባ ምክር ቤት፤ የመሰረተ ልማትና ማዘጋጀቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የፕሮጀክቶች እንቅስቃሴ ላይ በማተኮር ሲያካሂድ የነበረውን የመስክ ምልከታ በማጠናቀቅ ግብረ-መልስ ሰጥተዋል።
ቋሚ ኮሚቴው ለሁለት ተከታታይ ቀናት ባካሄደው የመስክ ምልከታ፤ የአውቶቡስ ተራ – 18 ማዞሪያ እና የእንግሊዝ ኤምባሲ – 22 – ኤድናሞል የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ አፈፃፀም የሚገኝበትን ሁኔታ ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
ከዚህም በተጨማሪ ቋሚ ኮሚቴው በአራራት ሆቴል – ኮተቤ – ካራ መንገድ ላይ የሚቀርቡ የህዝብ አስተያየቶችን መሠረት በማድረግ የመስክ ምልከታ ያደረገ ሲሆን፤ መንገዱ ለፈጣን የአውቶቢስ መስመር አካቶ የተሰራና የBRT መሰመሩ አገልግሎቱ ባለመጀመሩ ምክንያት የተፈጠረ ችግር መሆኑን ከባለሙያዎች ማብራሪያ ለመረዳት ችሏል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳሲ የተከበሩ ዶ/ር ግዛቸው አይካ በማጠቃለያ መድረኩ ላይ እንደገለጹት ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በስሩ ያሉ በርካታ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማብቃት መቻሉ ትልቅ ውጤት መሆኑን ገልጸው ፤ ይህም ተቋሙ በመልካም አፈጻጸም ላይ እንዳለ አመላካች መሆኑን ገልጸዋል።
በግንባታ ላይ የሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶች በፍጥነት ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ፤ በሚመለከታቸው አካላት መካከል ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሙህዲን ረሺድ በበኩላቸው፤ የመሰረተ ልማትና ማዘጋጀቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በየጊዜው የሚያደርገው ሱፐርቪዥን በፕሮጀክቶች አፈፃፀም ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮች እንዲፈቱ የበኩሉን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው፣ ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ከዳር እንዲደርሱ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር (X) ፡- https://twitter.com/AbabaCity
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ
