+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ቃላችንን በተግባር ለመፈፀም እንድንችል የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን!

በአንድ ጊዜ አንድ ሺሕ መኪኖችን የማቆም አቅም ያለውን እና በሾላ ገበያና መገናኛ መካከል ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ የሚያቃልለውን የካ ቁጥር 2 የመኪና ማቆሚያን መርቀን አገልግሎት አስጀምረናል::

ይህ የመኪና ማቆሚያ ከምድር በላይ ባለ አምስት ወለል እንዲሁም በመሬት ውስጥ ባለ ሁለት ወለል በጥቅሉ 8 ወለል ያለው ምቹ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት እንዲሁም የህዝባችንን እንግልት የሚያቃልል ነው::

የመኪና ማቆሚያው የህዝባችን አገልግሎት ምቾትና ክብርን የጠበቀ፣ ተገልጋዮችን ከዝናብና ፀሃይ የገላገለ ፣ የንፅህና መጠበቂያ ያለው፣ የሰው እና የመኪና አሳንሰር ያለው፣ ለአካል ጉዳተኞች አካታች የሆነ አገልግሎት የሚሰጥ፣ ሶስት የመኪና ማጠቢያ ስፍራ ያለው እንዲሁም ለነዋሪዎች የስራ እድል የሚፈጥር ግዙፍ ፕሮጀክት ሲሆን ሌሎች አገልግሎቶችን የሚሰጡ ሱቆች እና ቢሮዎች ያሉት የኢኮኖሚና የማህበራዊ አገልግሎትን ለማሳለጥ እንዲሁም የትራንስፖርት ስርአቱን ለማዘመን ትልቅ አስተዋጽዖ ያለው ነዉ።

የተሽከርካሪ ማቆሚያው ለመጀመሪያ ጊዜ በህንጻ ደረጃ የተገነባ ሲሆን መሬት እና በጀት በመመደብ የተሰራው ይህ ስራ ከተማችንን እንደ ስሟ ውብ አበባ የማድረግ አካል ነው::

ከለውጡ በፊት በመንግስት የተገነቡ የፓርኪንግ ቦታዎች ብዛት 2 ሲሆን 500 በላይ መኪኖችን የማቆም አቅም ያልነበራቸው እንዲሁ 1 ተርሚናል ብቻ የነበረዉን ከለውጡ በኃላ በሰራነው ስራ 150 የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን የገነባን ሲሆን የዛሬውን ጨምሮ 35 ሺሕ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ ማቆም የሚችሉ እንዲሁም 49 የሚደርሱ ተርሚናሎችን ገንብተን የትራንስፖርት ስርዓቱን ለማዘመን በመስራት ላይ እንገኛለን::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እናህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Comments are closed.