የቀለበት መንገድ የጥገና
ግንቦት 13 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት ከሚያስተናግዱ የከተማዋ መንገዶች አንዱ በሆነው የውስጠኛው ቀለበት መንገድ ላይ የተጎዱ ቦታዎችን በመለየት የአስፋልት ጥገና እያካሄደ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የከተማዋን ጎዳናዎች ለትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ ለማድረግ ባለፉት ወራት ወቅታዊና መደበኛ የመንገድ ጥገና ሥራ ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፤ አሁን ላይ ከቃሊቲ ማሰልጠኛ ወደ ካዲስኮ መስቀለኛ የሚወስደውን የቀለበት መንገድ ክፍል በአስፋልት ማልበስ እየጠገነ ይገኛል፡፡
በቀለበት መንገዱ የመሐል እና የዳር ክፍሎች ላይ የተጐዳውን የአስፋልት ክፍል ለይቶ በማንሳት 1 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር ርዝመት በ7 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን የጥገና ስራ አከናውኗል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር (X) ፡- https://twitter.com/AbabaCity
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ
