ከጃፓን መንግሥት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ማሽነሪዎችን የስራ እንቅስቃሴ የሚቃኝ ምልከታ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም፡- ለአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ጥገና አገልግሎት እንዲውሉ ከጃፓን መንግሥት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ማሽነሪዎች የስራ እንቅስቃሴ፤ በኢትዮጵያ የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ተወካዮች በተገኙበት የመስክ ምልከታ ተካሂዷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ፤ በጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ በኩል የተገኙ ማሽነሪዎች፤ በከተማዋ የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ስራዎችን በላቀ ደረጃ እንዲፈፀም እና የትራፊክ እንቅስቃሴው የተሳለጠ እንዲሆን ከፍተኛ እገዛ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት ከጃፓን መንግሥት በተገኘ ከ360 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ 97 የተለያዩ ማሽነሪዎችን በመጠቀም፤ ቀደም ሲል በዓመት 113 ኪሎ ሜትር የነበረው የመንገድ ጥገና ሽፋን ወደ 140 ኪሎ ሜትር ማሳደግ መቻሉን ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የጃፓን መንግሥት በትምህርት እና በቴክኖሎጂ የሚያደርገው ድጋፍ የተሻለ የመንገድ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል እገዛን እያበረከተ መሆኑን እና ወደፊትም ትብብሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ዳይሬክተሩ እምነታቸው ገልፀዋል። ፡፡
በኢትዮጵያ የጃይካ ተወካይ ሽንታሮ ታካሮ በበኩላቸው፤ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከጃፓን መንግሥት ያገኘውን የማሽነሪዎች ድጋፍ ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ በማዋል የከተማዋን የመንገድ ሽፋን ለማሳደግ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው፤ በቀጣይም የጃፓን መንግሥት በሁሉም ዘርፍ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር (X) ፡- https://twitter.com/AbabaCity
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ
